Company News
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲ የፕሮጀክት አፈጻጸም ግምገማ
የማማከር ድርጅታችን በቅርብ ክትትልና በውል አስተዳደር ሥራዎች ምክንያት በአሁኑ ወቅት ሁለት ንቁ ፕሮጀክቶች አሉት። እነሱም የማህበረሰብ ትምህርት ቤት (Community School) እና የዋናው ግቢና የጤና ግቢ ዋና በር እና አጥር (Main Campus and Health Campus Main Gate and Fence) ፕሮጀክቶች ናቸው።የማህበረሰብ ትምህርት ቤት ፕሮጀክት ለጊዜያዊ ርክክብ (Provisional Acceptance) የበቃ ሲሆን፥ ቀሪው ፕሮጀክት በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል። በተጨማሪም የዋናው ግቢ የአስፋልት መንገድ እና የአነስተኛ ድልድይ አካላት ዲዛይን ስምምነት ሥራዎችን ጀምረናል።